News

Previous Next

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በአውሮፓ

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በ15 ሀገራት ለተወከሉ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች እና የዳያስራ ዲፕሎማቶች ያዘጋጀው የሁለት ቀናት ዎርክሾፕ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ በሁለተኛው ቀን ውሎበ Governance and Community Mobilization በአውሮፓ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሁኔታ አንፃር የመወያያ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን በፅሁፉ ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ 

ከየሀገራቱ የተወከሉት የሚሲዮን መሪዎችና ዲፕሎማቶች በሶስት ቡድን ተከፍለው በየሀገራቸው ስላለው የዳያስፖራ ማሕበረሰብ ሁኔታ እና አቅም፣ ማሕበረሰቡን በማሳተፍና በማስተባበር ስላሉ ጥረቶች፣ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች የቡድን ውይይት አድርገዋል፡፡ ከውይይቱ በአውሮፓ ደረጃ የዳያስፖራ ማሕበረሰብ ልማት ስራዎቸ፣ የዳያስፖራ ተሳትፎን የማሳደግ ጥረቶች በምን መልኩ ሊመራና የሚጠበቀውን ሀገራዊ ራዕይ ማሳካት እንደሚቻል ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም በሚሲዮኖች መካከል የልምድ ልውውጥ የሚደረግባቸው መልካም ተሞክሮዎች እና የዳያስፖራ ኤጀንሲ ካስቀመጠው መዋቅርና ተልዕኮ አንፃር ከዚህ በኋል ስለሚኖረው አሰራር አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡