News

Previous Next

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከተቋቋመ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኦገስት 27-29፣ 2019 ለማክበር ታቅዶ የነበረው የዳያስፖራ ሳምንት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ።

 

በበዓሉ ላይ ኤግዝቢሽን የሚያቀርቡ  አካላት በቂ የዝግጅት ጊዜ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው፣ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማካሄድ በቂ የዝግጅት ጊዜ መወሰድ እንዳለበት በመታመኑና በሌሎችም ተያያዥ ምክንያቶች አከባበሩ እንደተራዘመ ከበዓል ዝግጅት ኮሚቴ ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

 

ሆኖም አስፈላጊ ዝግጅቶች ከተጠናቀቁ በኋላ አዲሱን የአከባበር ቀን ወስኖ እንደሚያሳውቅ ኮሚቴው አክሎ ገልጿል

Previous Next

ከስምንት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 18 የዳያስፖራ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገለጸ።

ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ፕሮጀክቶቹ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በሪልስቴት፣ በጤና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በንግድ ላይ የተሰማሩ ናቸው። በአጠቃላይ በፕሮጀክቶቹ አማካኝነት 845,776,457 ብር ኢንቨስት የተደረገ ሲሆን፣ ማኑፋክቸሪንግ በ365,586,000፣ ሆቴልና ቱሪዝም በ161,481,000 እንዲሁም ሪልስቴት በ150,000,000 በቅደም ተከተል ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። ፕሮጀክቶቹ ከ1200 በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደፈጠሩም ለማወቅ ተችሏል።

በከተማ አስተዳድሩ ወደ ስራ ከገቡት 18 ፕሮጀክቶች በተጨማሪ 1.2 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ 23 የዳያስፖራ ፕሮጀክቶች በሂደት ላይ  እንደሆኑ ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Previous Next

#Ethiopiansiasporaagency 

A three-day international conference on interdisciplinary research studies under the theme "Bring Minds together- Bridge the Gap" kicks off at African Union headquarters in Addis Ababa today.

 
The conference aims, among other things, to promote a dialogue among scholars and practitioners; provide a venue for academicians, scholars and policy makers to share their knowledge and contribute to bridge the gap in knowledge and understanding between the academic, private and public sectors.

Spearheaded by TASFA (Teach and Serve for Africa), an Ethiopian Diaspora volunteers' organization, the conference was sponsored by Ethiopian Diaspora Agency and other pertinent government organizations. 
 
It was learnt that separate events will be held in the coming two days to deliberate on eight different topics.

ከኦገስት 27 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሳንምት አስመልክቶ ተቀማጭነቱን በአሜሪካን ሃገር ያደረገው ‘ቲጂ ኢትዮጵያን ቲሌቪዥን’ ሰፊ ዘገባ አቀረበ። ዝርዝሩን ከቪዲዮው ይመልከቱ።

Previous Next

ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ቡድን በእስራኤል ሶስት ቀናት የፈጀ የቢዝነስ ጉባኤ አካሄደ።

ሁነቱ በእስራኤል በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊያን አነሳኝነትና በእስራኤል መንግስት ትብብር የተዘጋጀ ነበር። መርሃግብሩ እውን እንዲሆን ከማቀድ ጀምሮ የእስራኤል መንግስትን እስከማሳመን ያለውን  ስራ የተወጡት በሃገሪቱ ፓርላማና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙ በልጅነታቸው ከኢትዮጵያ የወጡና እዛው የተወለዱ ትውልደ ኢትጵያዊ እስራኤላዊያን ሲሆኑ ዓላማቸውም በኢትዮጵያና በእስራኤል መንግስታት መካከል በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በሳይበር ቴክኖሎጂ እንዲሁም በግብርና መስኮች ላይ ትብብር እንዲፈጠር ማድረግ ነው።

በመርሃግብሩም ላይ ከግብርና፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ  እንዲሁም ከውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስቴር፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው በሃገሪቱ ስላሉት አጠቃላይ የቢዝነስ ዕድሎች ማብራሪያ ከመስጠታቸውም በላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራትም ላይ በዋና ዳይሬክተሯ / ሰላማዊት ዳዊት ገላጻ ተደርጓል።

በመድረኩ የተሳተፉ አካላት ባነሷቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ላይ ምላሾችና ማብራሪያዎች በሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ከተሰጡ በኋላ መድረኩ ሐምሌ 24 2011/ በስኬትና በመግባባት መንፈስ ተጠናቋል።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እያከናወኗቸው ያሉ የበጎ አድራጎት ተግባራት የሚዲያ ትኩረት እየሳቡ ነው፡፡ ከዚህም   በተያያዘ  በቅርቡ አርትስ ቴሌቪዠን ያቀረበውን ዘገባ እንድትከታተሉ ጋብዘናችኋል፡፡ 

Previous Next

በሀገር ቤት የሚገኙ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን በማስተባበር በአረንጓዴ አሻራ ደማቅ ተሳትፎ እየተደረገ ነው። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በሁሉም አካባቢዎች የሚካሄዱ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሞችን በማሰተባበርም በመሳተፍም ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር፣ የአዲስ አበባ ዳያስፖራ ማህበር፣ የወጣት ዳያስፓራ ማህበርና በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት በጊንጪ ከተማ ደንዲ ወረዳ ጪለሞ ደን በተዘጋጀው 10000 ችግኝ ተከላ ላይ በሰፊው ተሳትፈዋል።. የዳያስፖራ አባላቱ መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል በማድረግ ወደስፍራው በጋራ ያቀኑ ሲሆን በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተሳትፈዋል። ይኖሩበት በነበረው ሀገር የሚያዩት አረንጓዴ ልምላሜ በሀገራቸውም እውን ሆኖ ለማየት የራሳቸውን አሻራ ማሳረፋቸው ደስታ እንደፈጠረባቸውና ስራውን በቀጣይነት ለመስራትም መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገልፀዋል።

በኦሮሚያ ክልል የኦሮሚያ ዳያስፖራ ማህበር በለገጣፎ አባላቱን በማሳተፍ የችግኝ ተከላ አካሂዷል። በትግራይ ክልል ከሀምሌ 24 ጀምሮ የሚከበረውን የክልሉን የዳያስፖራ ቀን በማስመልከት ሀምሌ 26 ለበአሉ ከመላው አለም የመጡ የዳያስፖራ አባላት የችግኝ ተከላ ያካሂዳሉ። በአማራ ክልል በዛሬው እለት የዳያስፖራ አባላቱ በተለያዩ አካባቢዎቸ እየተሳተፉ ይገኛል። በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ የዳያስፖራ ተሳትፎዎች እየተደረጉ ነው።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የዳያስፖራ ተሳትፎን ከተለመዱት እሳቤዎች ከፍ በማድረግና የነበሩ ውስንነቶችን በማሻሻል ተሳትፎን የሀገራችን ሁለንተናዊ ጉዳይን እንዲሸፍን በመስራት ላይ ነው።

Previous Next

ሁለተኛ ትውልድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ልጆች ውጤታማነትን ከአንደኛው ትውልድ የዳያስፖራ አባላት መስማት የተለመደ ጉዳይ ነው። ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ህብረት ተካሂዶ በነበረውና ’TASFA’ በተባለ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ቡድን በተዘጋጀው የዕውቀት ሽግግር ኮንፈረንስ ላይ ልምዳቸውን ያጋሩት የቡድን መሪው ዶ/ር ደረጀ ተሰማ እንዳሉት ሁለተኛ ትውልድ የኢትዪጵያ ዳያስፖራ አባላት ልጆች ውጤታማነት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በምሳሌነት የጠቀሱትም እሳቸው በሚኖሩበት ሞንትጎመሪ ካውንቲ በሚገኝ ት/ቤት ውስጥ ኢትዮጵያውያን የሁለተኛው ትውልድ ልጆች እያስመዘገቡት ያለውን ከፍተኛ ውጤት ነው። በእርሳቸው ዕምነት የወደፊቱን የአሜሪካ ጉዳይ ከሚወስኑ ሰዎች መካከል ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል።

የዶ/ር ደረጀን ምስክርነት ያነሳሁት በምክንያት ነው። ከአንድ ታዳጊ ወጣት ጋር ላስተዋውቃችሁ ስለፈለግሁ። ከልጁ ጋር የተገናኘነው በአትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ቢሮ ውስጥ ነበር። አመጣጡም የህይወቱ አርአያ ካደረጋቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር የሚገናኝበት ዕድል እንድንፈጥርለት ነው። ስሙ ራያን ሻሚ ይባላል። የተወለደው በካናዳ ነው። ዕድሜው ስምንት ሲሆን ሴንት ማቲው-ኬሲ ሬብልስ ለሚባል የሆኪ ቡድን በአጥቂ ስፍራ በመጫወት ላይ ይገኛል። በተያዘው የፈረንጆች አመት 2019 በክዊካርድ የኤድመንተን ታዳጊዎች የሆኪ ሳምንት የወርቅ ሜዳልያ ከተሸለሙ ስምንት ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው። ራያን ትልዕቅ ህልም ያለው ልጅ ነው። ህልሙ እንደሚሳካለትም አናምናለን። ባይወለድባትም የወላጆቹ ሀገር ለሆነችው ኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር አለው። መሪዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድንም በጣም ከማድነቁም በላይ በቡድናቸው መጽሔት ላይ አርአያው እንደሆኑ ገልጿል። ገና በታዳጊነቱ ለወላጆቹ ሃገር ከፍተኛ ፍቅር በማሳየት ላይ የሚገኘው ይህ ልጅ በሆኪ ስፖርት ዕውቅናው እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት ኢትዮጵያን በተሻለ ሁኔታ ማስጠራት እንደሚጀምር አያጠያይቅም።

Previous Next

ከስዊድን ሃገር መጥተው  በሶስት የበጎ አድራጎት ተቋማት  ተሳትፎ ላደረጉ የ’’እንብላ’’ ፕሮጀክት ቡድን አባላት የምስጋና የእራት ግብዣና የማስታወሻ ስጦታ ተደረገ።

ከስዊድን ሃገር ለበጎ አድራጎት ተግባር ተሰባስበው የመጡ ሁለተኛው ትውልድ ሰላሳ ሴት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ለሁለት ሳምንታት ያህል በተመረጡ ሶስት የበጎ አድራጎት ተቋማት በመገኘት ነጻ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል።  የኢትዮጵያውያን አብሮ የመብላት ባህል አብሮ የመስራትና የመተባባር ተምሳሌታዊ ትርጉም እንዳለው የሚያምኑት አባላቱ፣ በተቋማቱ በመገኘት ከሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተጨማሪ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍም አድርገዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለፕሮጀክት ቡድን አባላቱ የማስታወሻ ስጦታ ያበረከቱት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የ’’እንብላ’’ ፕሮጀክት ቡድን አባላት ላሳዩት ተነሳኝነትና የሃላፊነት መንፈስ አመስግነዋል። አክለውም የቡድን አባላቱ ካላቸው ተነሳሽነት አንጻር ወደመጡበት ሀገር በሚመለሱበት ወቅት ተጨማሪ የሁለተኛው ትውልድ ዳያስፖራ አባላትን እንደሚያሰባስቡና የተሻለ አቅም ፈጥረው በቀጣይ አመት እንደሚያገኟቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የፕሮጀክት ቡድን አባላቱም አቅማቸው በፈቀ መጠን በመስራት ተጨማሪ አባላትን ለማፍራትና ከሃገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።

Previous Next

A dinner party was held at Hilton Hotel in honor and appreciation of TASFA (Teach and Serve for Africa) members for the service and commitment they showed to their beloved country.

TASFA, an Ethiopian Diaspora volunteers' organization, composed of Ethiopian diaspora living in North America and Europe have been sharing their knowledge and experience in the areas of ICT, Engineering and Transportation, Hospitality and Tourism, among others. Having the motto ‘Transforming Government Efficiency through Knowledge Exchange’, they have trained hundreds of public servants and government officials.

 

In her remark during the event Mrs Selamawit Dawit, Director Genaral of Ethiopian Diaspora Agency, has appreciated the commitment and spirit of the team. She also added that the knowledge and experience of the diaspora have a paramount importance in the realization of a better Ethiopia. On his part,  Dr.-Ing. Getahun Mekuriya, guest of honor and Minister of Ministry of Innovation and Technology, has stressed the importance of diasporas’ role in the development of qualified manpower. Dr Dereje Tessema, team leader of TASFA, also reiterated that the diaspora understand their role and obligation to their country of origin. He mentioned that compared to the potential of the diaspora, his team’s effort is just tip of the iceberg. He also promised that his team will do the same and more in the coming times.

 

Previous Next

 

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የዳያስፖራ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ያሉ ማነቆዎችን መፍታትን ዒላማ ያደረገ የባለድርሻዎች የሁለት ቀናት የምክክር መድረክ በአዳማ አካሂዷል። በምክክር መድረኩ ላይ ከዘጠኙ ክልሎቸ እና ሁለት የከተማ መስተዳድሮች የዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች፣ የዳያስፖራ ማሕበራት አመራሮች፣ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ የዳያስፖራ ባለሀብቶች፣ በፌዴራል መስሪያ ቤቶች የዳያስፖራ ጉዳይ ላይ በኃላፊነት የሚሰሩ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ማነቆዎች የመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሁሉም ባለድርሻዎች ሚና ምን መሆን እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል። 

Previous Next

ሁለተኛው ዓለም ዓቀፍ የትግራይ ዳያስፖራ ፌስቲቫል በመቀሌ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል። 

በትግራይ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ የሚገኘውና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በተገኙበት የተከፈተው ፌስቲቫል ከሐምሌ 24-30፣ 2011ዓ/ም ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል።

ለፌስቲቫሉ ድምቀትና ስኬታማነት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከክልሉ ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር አብሮ የሰራ ሲሆን፣ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እንድሪስም ለፌስቲቫሉ ታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁና የአጋርነት መልዕክት አስተላልፈዋል። 

አቶ መሐመድ አክለውም ኤጀንሲው የተሻላ የዳያስፖራ ሀገራዊ ተሳትፎን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል። 

በፌስቲቫሉ ከታቀፉ መርሃ ግብሮች መካከል ከሁለት ሺህ በላይ ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ የዳያስፖራ አባላት የተሳተፉበት  በሀገራዊና በዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳይ ላይ ያተኮረ

 ሲምፖዚየም፣ የ''አረንጓዴ አሻራ'' የችግኝ ተከላ፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ እና መሰል የልማት ተቋማት ጉብኝቶች የተካሄዱ ሲሆን፣ በቀሩት ቀናትም መርሃ ግብሩ ልዩ ልዩ ሁነቶችን በማስተናገድ እንደሚቀጥል ታውቋል።

 

 የክልሉ የዳያስፖራ ፌስቲቫል ለመጀመሪያ ጊዜ በ2006ዓ/ም መከበሩ ይታወሳል።